0:10
ለተከታታይ ቀናት በርካቶች አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ፌዴሬሽን ኤምባሲ ፊት ለፊት ተሰልፈው ታይተዋል። ቢቢሲ ከኤምባሲው ፊት ለፊት ተሰልፈው ከነበሩት መካከል ያነጋጋራቸው ወጣቶች፤ በሩሲያ ያለ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን እና የሥራ ቅጥሩ ክፍያ ከፍተኛ መሆኑን በመስማታቸው በስፍራው መገኘታቸውን ተናግረዋል። የተቀሩት ደግሞ ሞስኮ ከዩክሬን ጋር ለምታደርገው ጦርነት በውትድርና የመቀጠር ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል። ቢቢሲ ኤምባሲው በር ላይ ተሰልፈው ከሚገኙ ሰዎች ተጨማሪ አስተያየቶችን መስማት ይፈልጋል። በውስጥ መልዕክት ስልካችሁን ብትተዉልን መልሰን እንደውላለን። እናመሰግናለን። ከዚህ በታች የሚታየው ምሥል ዛሬ ሚያዚያ 11/2014 ዓ. ም. ከሩሲያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተወሰደ ነው። | BBC News Amharic
217.4K viewsApr 19, 2022
FacebookBBC News Amharic
3:28
"የመጀመሪያ ሥራዬ ቤተ እስራኤላዊያንን ወደ አገራቸው ማምጣት ነው" ቤተ እስራኤላዊቷ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሚንስትር *********************************************************************************************************************************** እስራኤል በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን ጥቁር ሚንስትር ሾማለች። አዲስ ተሿሚዋ ሚንስትር ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ "የመጀመሪያ ሥራዬ ቤት እስራኤላዊያንን ወደ አገራቸው ማምጣት ነው" ብለዋል። በአጠቃላይ በጥቁር ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን በደልና አድልዖ እንደሚታገሉና በመንግሥታቸው ላይ ጫና እንደሚያሳድሩም ተናግዋል። https://bbc.in/2YtmmQ1 | BBC News Amharic
38.4K viewsJun 24, 2020
FacebookBBC News Amharic
2:58
በናይሮቢ የታፈነው የሳምሶን ባለቤት ጉዳዩ እጅጉን አሳስቦኛል አለች ከቀናት በፊት በኬንያ ናይሮቢ የታፈነው ኢትዮጵያዊ ሳምሶን ተ/ሚካኤል ጉዳይ እጅጉን እንዳሳሰባት ባለቤቱ ሚለን ሃለፎም ለቢቢሲ ተናግራለች። የባለቤቷን መታፈንን ተከትሎ ለኬንያ ፖሊስ እና ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን ማሳወቋን የምትናገረው ሚለን፤ ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትብብር እያደረገለት እንደሆነ ገልጻ "የኬንያ መንግሥት ግን እየተባበረ አይደለም" ብላለች። የኬንያ ፖሊስ በበኩሉ ጉዳዩን እየተከታተለው እንደሆነ ገልጿል። | BBC News Amharic
1.3M viewsNov 24, 2021
FacebookBBC News Amharic
See more